AAU 2011 Call for Summer Voluntarism
የክረምት በጎ ፈቃድ ስራዎች ጥሪ
ዩኒቨርስቲያችን ከሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ‘የ2011 ክረምት በጎ ፈቃድ የሚሰሩ ስራዎች እንዲሰሩ እቅድ አውጥቶ ተማሪዎች እንደየፍላጎታቸው በሚመርጡት አካባቢ
- በአካባቢና ተፈጥሮ ኃብት ጥበቃ፤ በችግኝ ተከላ፣ (በተለይ ተመራቂ ተማሪዎች ከምርቃት በፊት በሚወጣ መርኃግብር የሚያከናውኑት)፤በአካባቢ ጽዳት
- በጤና ዘርፍ፤ የህብረተሰብ ጤና ግንዛቤ ማስጨበጥ (ለምሳሌ HIV/AIDS, ኮሌራ)
- በሰብዓዊ ዘርፍ፤ አቅመ-ደካሞችን በመደገፍ
- ትምህርት ዘርፍ፤ ተማሪዎችን የክረምት ቲቶሪያል ትምህርት በማስተማር፤ የኮሚፒዩተር ስልጠና በመስጠት
- በስፖርትና ስነጥበብ፤ ስፖርታዊ አሰልጣኝነት፤ ድራማ፤ ውዝዋዜ፤ ስዕልና ሌሎችንም ስልጠናዎችን
- በደም ልገሳ፣እና በሌሎችም ዘርፍ
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለመስጠት በየተማሪዎች ህብረት ተወካይ አማካኝነት እስከ ሰኔ 28 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ እንድትመዘገቡ ጥሪ እናቀርባለን፡፡
ማሳሰቢያ፤ 1)ተማሪዎች ለበጎ ፈቃድ አገልግሎት በወረዳቸው ያለ የወጣቶች ማህበር አደረጃጀት/የወጣቶች ሴቶችና ህጻናት ጽ/ቤት ሪፖርት ማድረግ አለባቸው
2) የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱን በሚገባ ያጠናቀቀ ተማሪውን ለወደፊቱ ለስራ ቅጥር የሚያግዝ የእውቅና ሰርተፌኬት ይዘጋጅለታል፡፡
ከታች መመዝገቢያ በተያያዘው ሊንክ ይመዝገቡ
የማህበረሰብ ተሳትፎ ጽ/ቤት