የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሴኔት አባላት፣አካዳሚክ፣አስተዳደር ሰራተኞች በሙሉ
ውድ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሴኔት አባላት፣አካዳሚክ፣አስተዳደር ሰራተኞች በሙሉ
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ባለፈው አርብ ህዳር 17 ቀን 2014 ዓ.ም. የሴኔት ጉባኤ አባላት፣ ሁሉም ዲኖችና ዳይሬክተሮች በፕሬዝዳንቱ ሰብሳቢነት በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይ ላይ ተወያይተው ምሁራዊና ኢትዮጵያዊ ወገንተኝነታውን በአቋም መግለጫቸው ማሳየታቸው አይዘነጋም፡፡
በተጨማሪም አሜሪካና አንዳንድ የአውሮፓ ሃገራት በኢትዮጵያ ላይ እያደረጉት ያለውን አላስፈላጊ የውስጥ ጣልቃ-ገብነትና ጫና ለመቃወም የሚያስችል መድረኮች እንዲያመቻች አራት አባላት ያሉበት ኮሚቴ ተቋቁሟል፡፡ በመሆኑም በመጪው ሐሙስ ህዳር 23 ቀን 2014 ዓ.ም. ወደ አሜሪካን ኤምባሲ በጸጥታ የሰላማዊ ሰልፍ (silent march) ለማድረግ ስለታቀደ ሁሉም የዩኒቨርስቲው ማኅበረሰብ (የሴኔት አባላት፣ አካዳሚክና የአስተዳደር ሠራተኞች) ከጠዋቱ 1፡30 ላይ በራስ መኮንን አዳራሽ (IES) ፊት ለፊት እንድትገኙ ዩኒቨርስቲው አገራዊ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
የኮሌጅ ዲኖችና ዳይሬክተሮች በውስጣችሁ ያሉትን ትምህርት ክፍሎች በማስተባበር አስፈላጊውን ትብብር እንድታደርጉ እየጠየቅን ቢቻል መምህራን የማስተማርያ ጋዋን ለብሰው እንዲገኙ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
የፕሬዚደንት ጽ/ቤት