Announcement for Evening Undergraduate program applicants
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2012 ዓ.ም. በማታ መርሃግብር ለመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት አመልካቾችን ይጋብዛል
በዚህም መሰረት አመልካቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል
- በዲግሪያችሁ ለምታመለክቱ 40 ብር በመክፈል የወጪ መጋራት ያጠናቀቃችሁበትን የሚገልፅ ደብዳቤ ከትምህርት ማስረጃ ማቅረብ፤
- በዲፕሎማችሁ ለምታመለክቱ150 ብር በመክፈል ከትምህርት ማስረጃ ጋር የCOC ደረጃ 3 ወይም 4 ማቅረብ
- ዲፕሎማችሁ የአስተማሪነት ሆኖ ለምታመለክቱ 150 ብር በመክፈል ዲፕሎማ በጨረሳችሁበት የትምህርት አይነት ብቻ በመመዝገብ የትምህርት ማስረጃ ማቅረብ
- ለPreparatory አመልካቾች ከ2004-2011ዓ.ም. ድረስ ብቻ ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መስፈርት መሰረት ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብን የምታሟሉ 40 ብር በመክፈል ከትምህርት ማስረጃ ጋር በማያያዝ ማቅረብ
- ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች በተለያየ ምክንያት አቋርጣችሁ ለምታመለክቱ የወጪ መጋራት ያጠናቀቃችሁበትን የሚገልፅ ደብዳቤ 40 ብር በመክፈል ከትምህርት ማስረጃ ጋር በማያያዝ ማቅረብ
- ለያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት እና ለአለ ፈለግ ስእል ትምህርት ቤት በቀን መርሃ ግብር ማመልከት የሚችሉት
በPreparatory ከ2004-2010 ዓ.ም. ተምረው የጨረሱና ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መስፈርት መሰረት ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብን አምጥተው ለነበሩ የወጪ መጋራት ክፍያ ያጠናቀቁበትን ደብዳቤ ከትምህርት ማስረጃ ጋር ማያያዝ፡፡
የምዝገባ ቀን
ከነሐሴ 20 እስከ ጳጉሜ 1 2011 ዓ.ም
የምዝገባ ቦታ
በሬጅስትራር ህንፃ ቢሮ ቁጥር 203
የክፍያ ቦታ
ከሬጅስትራር ህንፃ ቢሮ ቁጥር 7 ወይም 8
ማሳሰቢያ፡-
- አመልካቾች በዩኒቨርስቲው ድረ-ገጽ (portal.aau.edu.et) ላይ ማመልከትና የመመዝገቢያ ቁጥሩን በመያዝ የትምህርት ማስረጃ አንድ ኮፒ ከአንድ ጉርድ ፎቶግራፍ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በዲፕሎማ አመልካቾች የዩኒቨርስቲውን የመግቢያ ፈተና ጊዜን ፤ የትምህርት ክፍሎቹን ዝርዝር እና ተጨማሪ ማብራሪያ ከዩኒቨርስቲው ድረገጽ (www.aau.edu.et) እና (www.portal.aau.edu.et) ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ያሳውቃል፡፡
አአዩ ሬጅስትራር