Announcement for Non Graduating Undergraduate Students
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቅድመ ምረቃ መደበኛ እና የማታ ፕሮግራም ተማሪዎች (ከ1ኛ አመት ጀምሮ ለሆናችሁ ሁሉ)
በኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የተቋረጠዉ የ2012 ዓ.ም የሁለተኛ ሰሚስተር ትምህርት ለማስጀመር የመልሶ ምዝገባ በሚከተለዉ መሠረት ይካሄዳል፡፡
- የማታ ተማሪዎች ምዝገባ ታህሳስ 10 እና 11 2013 ዓ.ም
- የመደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ ታህሳስ 21 2013 ዓ.ም ሲሆን
- ተመዝጋቢዎች ከኮሌጅ ሬጅስትራር ጽ/ቤቶች በመገኘት የኮርስ ምዝገባ ማካሄድ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የምዝገባ ወረቀቶቹ እንደ ተማሪ መታወቂያ ስለሚያገለግል በጥንቃቄ መያዝ ይኖርባችኋል፡፡
- ለመደበኛ ተማሪዎች ትምህርት መልሶ መከፈትን በተመለከተ እና ሊደረጉ ስለሚገቡ ጥንቃቄዎች ታህሳስ 22 ቀን 2013 ዓ.ም ገለፃ ይደረጋል፡፡
- ትምህርት የሚጀመረዉ ታህሳስ 23 ቀን 2013 ዓ.ም መሆኑን ያሳዉቃል
- ከምዝገባ በፊት ወይም በኋላ የሚመጡ ተማሪዎችን ዩኒቨርስቲዉ አያስተናግድም
- ዝርዝር መረጃዎችን ከዩኒቨርስቲዉ ድረ ገፅ http://aau.edu.et ማግኘት ይቻላል፡፡
አ.አ.ዩ ሬጅስትራር