Menu

Announcement for Summer in Service Trainees

በትምህርት ሚኒሰቴር ስፖንሰር ለተደረጋችሁ የአዲስ አበባ  ዩኒቨርሲቲ  የክረምት ተከታታይ ትምህርት ሠልጣኞች በሙሉ፤

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመስከረም 18 እስከ መስከረም 30 ቀን 2014 ዓ.ም. ባሉት ጊዚያቶች የክረምት ተከታታይ ትምህርት ፕሮግራም የሚያካሂድ መሆኑን እየገለጽን ከዚህ በታች በተዘረዘረው ምደባ መሠረት በየተመደባችሁባቸው ካምፓሶች በመገኘት ምዝገባችሁን አካሂዳችሁ ትምህርታችሁን እንድትከታሉ እናሳስባለን፡፡ የምግብ አገልግሎት እና ትምህርት የሚሰጠው በተመዳባችሁባቸው ካምፓሶች መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ በሰፈረ-ሰላም እና ልደታ ካምፓሶች የተመደባችሁ ሠልጣኞች ምዝገባ በየኮሌጃችሁ እንደሚካሄድ አውቃችሁ ምዝገባችሁን ማካሄድ አለባችሁ፡፡ በተጨማሪም በ2011 ዓ.ም. በተለያዩ ዘርፎች በዩኒቨርሲቲው ውስጥ በከረምት ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም የተሰጡትን ትምህርቶች አጠናቃችሁ የፒጂዲቲ (PGDT) ስልጠና ብቻ የቀራችሁ ሠልጣኖች በስነ-ትምህርት እና ባህሪ ጥናት ኮሌጅ ሬጅስትራር ጽ/ቤት በመገኘት ምዝገባችሁን እንድታካሂዱ እናሳስባለን፡፡

Summer In Services Training Program Trainees’ Campus Placement

S/No   Trainees in Program  of  Campus  Remark
1 ·         Afan Oromo, Amharic & English (BA & MA)

·         Special Needs Education (MA),

·         Early Childhood Care & Education  (MA)

 Main Campus ( 6 Kilo)
2 ·         Biology, Chemistry, Physics, Mathematics, & Library Sciences College of Natural  & Computational Sciences (4 Kilo)
3 ·         Civics & Ethical Education (BA & MA)

·         Special Needs Education (BA)

·         School Leadership (MA)

Lideta (EiABC) Campus
4 ·         History & Geography (BA & MA) Sefereselam, College of Health Sciences
5 ·         PGDT 2011 Entry

·         Sport Sciences  (BSc)

College of Business and Economics
6 ·         PGDT 2014 Entry Addis Ababa Institute of Technology (5 Kilo) This group  includes only  those summer in service program trainees who completed their undergraduate degree studies in their respective areas in AAU during 2011 E.C
7 Music &  Art  ( BA) College of Visual & Fine arts  Campus

 

ማሰሰቢያ

ወደ ዩኒቨርሲቲ ስትመጡ የመገጣጠሚያ ደብዳቤ ከሚመለከታቸው የትምህርት ቢሮዎች/ጽህፈት ቤቶች አጽፋችሁ መምጣት ይኖርባችኋል፡፡

ከተጠቀሰው ቀን ውጭ የሚመጡ ሠልጣኞችን አናስተናግድም፡፡

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ