Announcement for Undergraduate Program in the College of Humanities, Language Studies, Journalism and Communication
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሂዩማኒቲስ፣ ቋንቋዎች ጥናት፣ ጋዜጠኛነትና ኮሙኒኬሽን ኮሌጅ ለ2014 የትምህርት ዘመን በመደበኛ መርሃ-ግብር
ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የትምህርት መስኮች
- General Linguistics
- Ethiopian Sign Language
- አማርኛ
- ትግርኛ
- ፎክሎር
- English Literature
- Modern European Language
- Arabic
- French
ለመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት አመልካቾችን ይጋብዛል
የቅበላ መስፈርቶች፦
- አመልካቾች Preparatory በ2013 ዓ.ም. ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መስፈርት መሰረት ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብን የሚያሟሉ እና ከትምህርት ማስረጃ ጋር በማያያዝ ማቅረብ የሚችሉ
- ከላይ በተጠቀሱት መስኮች ተምረው ሃገራቸው ለማገልገል ፍላጎትና ዝንባሌ ያላቸው፣
- በማህበራዊ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ የዘመኑን የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች መግቢያ መቁረጫ ነጥብን ያሟሉ፣
- ማንኛውም የቅድመ ምረቃ መርሃ ግብር ተማሪ እንዲያቀርብ የሚጠየቀውን የትምህርት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- እንደአስፈላጊነቱ የትምህርት ክፍሎች የሚያዘጋጁትን ፈተና ለመቀበል ዝግጁ የሆኑ፣
- በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጡ ፍሬሽማን ኮርሶችን በሚመደቡበት የትምህርት ክፍል ውስጥ ሆነው ለመማር ፈቃደኛ የሆኑ፣
ማሳሰቢያ፡-
- የማመልከቻ ፎርሙን በዩኒቨርስቲዉ ድረ ገጽ (https:\\portal.aau.edu.et) መሙላት
- ከማመልከቻ ፎርም የሚያገኙትን የማመልከቻ ቁጥር (Application Number) በመያዝ ብር 150 / አንድ መቶ ሃምሳ/ በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ በሞባይል CBE ብር ወይም በወኪሎች ወይም በቅርንጫፍ አማካኝነት በ242424 አጭር ኮድ ክፍያ መፈጸም
- ክፍያዎትን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ማመለከቻ ፎርሙ በመመለስ በፒዲኤፍ (PDF) ፎርማት የተለወጠ የትምህርት ማስረጃዎትን የወጪ መጋራት ያጠናቀቁበትን ሰነድ መላክ፤
- ምዝገባዉ ካከናወኑ በኋላ የትምህርት ማስረጃ በአካል ይዞ በመቅረብ ቢሮ ቁጥር 203 ማስገባት ይኖርብዎታል፡፡
- የተማሪዎች ቁጥር ከመቀበል አቅም በታች (ዝቅተኛ) ከሆነ የትምህርት ፕሮግራሞች የማይከፈቱ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የምዝገባ ቀን፡ ከግንቦት 03 እስከ ግንቦት 10 2014 ዓ.ም
የምዝገባ ቦታ ፡ በሬጅስትራር ህንፃ ቢሮ ቁጥር 203
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሬጅስትራር