Biographical Profile of Dr. Abiy Kifle
Dr. Abiy Kifle Teklemariam was born in November 1940 in the town of Fitche, North Shoa, Ethiopia. He attended secondary education in the General Wingate Secondary School, Addis Ababa. In 1962 he graduated with a BSc degree in Mathematics from the College of Natural Science, Addis Ababa University (then called Haile Selassie I University). In 1965 he got his MSc degree in the same field of study from the University of Connecticut, U.S.A. After completing his studies, he came back to Addis Ababa University and served as a lecturer until1968. He then went to Uppsala University, Sweden, where he earned his PhD degree in 1971. He returned to AAU in September1971 to rejoin the Mathematics Department where he served as Acting Head and lecturer until April 1972. He also served the University at higher levels of the management including as dean of College of Natural Sciences and made valuable contributions to the institution. Among his contributions his book, entitled, ‘A First Course in Calculus, used in many universities in Ethiopia to date, as a textbook for Calculus One, the first course in mathematics, still keeps his memory alive among many students and academic staff in the country. He was an outstanding scholar who exhibited great caliber in his work and commitment to his duty. In October 1981, considering his outstanding academic quality and performance, he was appointed Academic Vice President of the University. In March 1985, taking into account his leadership quality and personal and professional experiences, he was appointed President of the Addis Ababa University, which he served until June1991. (Source: Human Resource Management Archive, AAU)
የዶ/ር ዐቢይ ክፍሌ አጭር የሕይወት ታሪክ
ዶ/ር ዐቢይ ክፍሌ ተ/ማርያም እአአ በ1940 በፍቼ ከተማ ሰሜን ሸዋ ተወለዱ፡፡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው በጀነራል ዊንጌት ት/ቤት እአአ እስከ 1958 ድረስ በመከታታል በማእረግ አጠናቅቀዋል፡፡ እአአ በ1962 ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጅ በሂሳብ ትምህርት የባችለር ኦፍ ሳይንስ ዲግሪ ተቀብለዋል፡፡ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ተቀጥረው ለጥቂት ጊዜ በመምህርነት ካገለገሉ በኋላ ለከፍተኛ ትምህርት ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ወደሚገኘው ከኔክቲከት ዩኒቨርሲቲ በመሄድ የሁለተኛ ዲግሪ ትህርታቸውን በመከታተል እአአ በ1965 በሂሳብ በማስተር ኦፍ ሳይንስ ዲግሪ ተመርቀዋል፡፡ ወደ ሀገራቸው ተመልሰው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለጥቂት ጊዜ በመምህርነት ካገለገሉ በኋላ እንደገና ለከፍተኛ ትምህርት ወደ አብሳላ ዩኒቨርሲቲ ስዊድን በመሄድ እአአ በ1971 የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ተቀብለዋል፡፡ ከዚያ ከተመለሱ በኋላ እአአ እስከ ሚያዝያ 1972 ድረስ በማቲማቲክስ ዲፓርትመንት በሌክቸረርነትና በዲፓርትመንት ሐላፊነት ቀጥሎም በተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጅ ዲንነት አገልግለዋል፡፡ ካደረጓቸው አስተዋፅኦዎች ውስጥ በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ለሂሳብ ማስተማሪያ እንዲሆን ያዘጋጁት ‘A First Course in Calculus’ የተሰኘው መጽሐፍ በሂሳብ ትምህርት የመጀመሪያውን ኮርስ ለማስተማር በሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች አገልግሎት ላይ የዋለ በበርካታ ተማሪዎችና መምህራን ዘንድ ሁልጊዜ ሲታወሱ እንዲኖሩ ያደረገ ሊጠቀስ የሚገባው ስራ ነው፡፡ እአአ በ1981 በስራ ያሳዩትን ጥረትና ውጤታማነት በመገምገም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ም/ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾመዋል፡፡ በተመሳሳይ በመምህርነትና በተለያዩ የሐላፊነት ቦታዎች ላይ የነበራቸውን የስራ አፈፃፀም በመገምገም እአአ በ1985 የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ሆነው የተሾሙ ሲሆን በዚሁ ከፍተኛ የአመራር ቦታ እአአ አስከ 1991 ድረስ በታማኝነትና በከፍተኛ ትጋት ዩኒቨርሲቲውን አገልግለዋል፡፡ (ምንጭ፤ ሰው ሀብት አመራር ቤተ መዛግብት፤ አአዩ)