Menu

ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ (ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንትነት)

AAU Logo

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉትን እና ዩኒቨርሲቲውን በፕሬዚዳንትነት ለመምራት ፍላጎቱና ብቃቱ ያላቸውን አመልካቾች አወዳድሮ የላቀ ውጤት ያመጣውን/ችውን ተወዳዳሪ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አደርጎ ለመመደብ ይፈልጋል፡፡

  1. ስለተቋሙ አጭር መግለጫ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ ፈር ቀዳጅ እና በአፍሪካም ሥመ ጥር ከሚባሉት ዩኒቨርሲቲዎች መካከል የሚመደብ፤ ከ50 ሺ በላይ ተማሪዎችን፣ ከ7ሺህ በላይ የሚሆኑ መምህራንን፣ ተመራማሪዎችንና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችን በመያዝ በርካታ የድህረ-ምረቃና የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞችን የሚያካሂድ፣ ትላልቅ ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸውን የምርምር ስራዎችን የሚያከናውን እንዲሁም ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸውን ማህበራዊ አገልግሎቶች የሚሰጥ አንጋፋና ግዙፍ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ነው፡፡

  1. የስራው መደብ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት

  1. ማመልከቻ መስፈርቶች

3.1 የትምህርት ደረጃ፡- ሶስተኛ ድግሪ (PhD) ወይም ሁለተኛ ድግሪ (MA/MSc) እና ቢያንስ የረዳት ፕሮፌሰርነት ማእረግ ያለው/ያላት፣

3.2 የሥራ ልምድ፡-  በከፍተኛ ትምህርት፣ በኢንዱስትሪ፣ በምርምር ተቋማት ወይም መሰል ተልዕኮ ባላቸው ተቋማት በከፍተኛ አመራር/ኃላፊነት እርከን ያገለገለ/ች

3.3 ስትራተጂያዊ እቅድ ማቅረብ፡- አመልካቾች በዩኒቨርሲቲው የከፍተኛ ትምህርትን ተደራሽነት፣ ፍትሃዊነት፣ ጥራት፣ ተገቢነትና ዓለምአቀፋዊነት ለማሳካት ስለሚከተሉት ስልት፤ ዩኒቨርሲቲውን የልህቀት ማዕከል ለማድረግ ስለሚሰጡት አመራር ከ10 ገጽ ያልበለጠ ስትራቴጂያዊ እቅድ በፅሁፍ ያቀርባሉ፤ ስላቀረቡት እቅድ ለዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ስታፍና ሰራተኞች እንዲሁም ተማሪዎች በሚዘጋጀው መድረክ ላይ ገለፃ ያደርጋሉ፤

3.4 እድሜ፡- አመልካቾች እድሜያቸው ከ65 ዓመት ያልበለጠ መሆን አለበት፤

3.5 ፆታ፡- ማስታወቂያው ወንዶችንና ሴቶችን የሚያጠቃልል ሲሆን፣ መስፈርቱን የሚያሟሉ ሴቶች ሁሉ እንዲያመለክቱ ይበረታታሉ፤

  1. ተፈላጊ ክህሎቶች

4.1 የአመራር ክህሎት፡- አመልካቾች በዩኒቨርሲቲው ያለውን የሰው፣ የገንዘብና የቁሳቁስ ሃብት በማስተባበር፣ ለመምራት የሚያስችል ዕቅድ በማቀድ፣ የአሠራር፣ የክትትል፣ የድጋፍና ቁጥጥር ሥርዓትን በመዘርጋት፣ ኃላፊነትንና ተጠያቂነትን በማስፈን የአካዳሚክና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞችን የሥራ ተነሻሽነትና የባለቤትነት ስሜት ለማሳደግና የዩኒቨርሲቲውን ተልዕኮና ራዕይ ለማሳካት የሚያስችል የአመራር ክህሎት ያላቸው መሆን አለባቸው፤

4.2 አዲስ አሰራር የመፍጠርና ለውጥ የማምጣት ክህሎት፡- አመልካቾች በዩኒቨርሲቲው ለውጥና እድገትን ለማምጣት የሚያስችሉ አዳዲስ የአሰራር ስልቶችን የማመንጨትና ተግባራዊ የማድረግ አቅም ያላቸው መሆን አለባቸው፤

4.3  የተግባቦት ክህሎት፡- አመልካቾች በዩኒቨርሲቲውም ሆነ ከዩኒቨርሲቲው ውጭ ካሉ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ አገራዊ፣ አህጉራዊና አለምአቀፋዊ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት በመፍጠር የዩኒቨርሲቲውን ተልዕኮና ራዕይ ለማሳካት  የሚያስችል የተግባቦት ክህሎት ያላቸው መሆን አለባቸው፣

  1. ተፈላጊ ሥነ-ምግባራዊ ባህርያት

5.1 አመልካቾች ከሥነ-ምግባር ጉድለቶች የፀዱ፣ በመልካም ባህርያቸውና በስራ አክባሪነታቸውና ታታሪነታቸው የተመሰከረላቸውና ለሌሎች አርአያነታቸው የጎላ መሆን አለባቸው፤

5.2 አመልካቾች ተግባብቶ የመስራት፣ ሁሉን በእኩል የማስተናገድ፣ ለሚቀርቡላቸው ጉዳዮች ተገቢውን ምላሽ በተገቢው ጊዜ የመስጠት መርህ የሚከተሉ መሆን አለባቸው፣

  1. የምደባ ሁኔታ

በውድድሩ የላቀ ውጤት በማምጣት የተመረጠው/ችው አመልካች አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ለስድስት አመታት በፕሬዚዳንትነት የሚመራ/የምትመራ ሲሆን የፕሬዚዳንትነቱ ጊዜ እንዳስፈላጊነቱ ሊራዘም ይችላል፤

  1. ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስኬል መሰረት፤

  1. የማመልከቻ ጊዜ

አመልካቾች ማመልከቻቸውን፣ CV እና ኦርጅናል የትምህርት እና የሥራ ልምድ ማስረጃቸውን እንዲሁም ከ10 ገጽ ያልበለጠ ስትራተጂያዊ እቅድ (ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር) ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ( ኅዳር 16 ቀን 2010) ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የስራ ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤

  1. የማመልከቻ ቦታ

አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት፣ አዲሱ አድሚኒስተሬሽን ሕንፃ፣ አንደኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 102፤

      10. የማመልከቻ ማቅረቢያ መንገዶች

10.1  በዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት በግንባር ቀርቦ በመመዝገብ

1ዐ.2 በዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ኢ-ሜይል አድራሻ poffice@aau.edu.et በመላክ

1ዐ.3 በፖስታ ሳጥን ቁጥር 1176 ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አድራሻ በመላክ

      11. ለተጨማሪ መረጃ በሚከተሉት መንገዶች መጠቀም ይቻላል

11.1  በዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ስልክ ቁጥር +251 1 11239752

11.2  በዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ሞባይል ስልክ ቁጥር +251 9 11 049970

11.3  በዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ኢ-ሜይል አድራሻ poffice@aau.edu.et

11.4  በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዌብ ሳይት portal.aau.edu.et

Download manuals and proclamations Below

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አመራር ቦርድ