Menu

Books Briefing

1

… ይህ መጽሐፍ በተለይ ለአማርኛ ቋንቋ አንባቢያን የግብረገብና ሥነ-ምግባር ፍልስፍናን የሚያስተዋውቅ ነው፡፡ ጸሐፊው ባነሷቸው ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ በቂ ምሁራዊ ይዘት ያላቸውን ግብአት ለማካተት ችለዋል፡፡ እንዲሁም ስለግብረገብ ፍልስፍና ያላቸው ዕውቀትና ይኸንንም ከዕለት ተዕለት ችግሮቻችን ጋር አሳንስው ለማየት ያደረጉት ሙከራ ከፍተኛ ዋጋ ያለው ነው፡፡ ይኽውም መጽሐፉን የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ከሞራል ፍልስፍና አንጻር ለመቃኘት የሚያስችል ስለሚያደርገው ለጠቅላላ አንባቢው ጠቀሜታ እንዲኖረው አድርጎታል፡፡

በቀለ ጉተማ (ዶ/ር)

በአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ

የፍልስፍና ትምህርት ክፍል

በሥነ-ምግባር ዙሪያ የተጻፈ ብዙ መጻሕፍት የሉም፡፡ ከዚህ አንፃር ይህ መጽሐፍ ዋጋው ላቅ ያለ ነው፡፡ መጽሐፉ ለሥነ-ልቦና አማካሪዎች፣ ለማኅበራዊ አደረጃጀትና ለሕብረተሰብ ግንኙነት ተመራማሪዎችም እንደጠቅላላ ንባብ እና ለተጨማሪ የምርምር ሐሳብ ማነሳሻ ይጠቅማል፡፡ በዚህ መልኩ መጽሐፉ በመስኩ ለሚፈልግ ጠቅላላ ዕውቀት ግንባታ ከሚኖረው አስተዋጽኦ በተጨማሪ የተጻፈበት ቋንቋ ሀገርኛ በመሆኑ፤ ተደራሽነቱ የሰፋ ይሆናል፡፡

ያዕቆብ አርሳኖ (ዶ/ር)

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል

ጠና ደዎ ሰው፣ ግብረገብና ሥነ-ምግባር የዘመናችን ቁልፍ ጉዳዮች አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ ISBN 9789994452729 ገጽ 502 ዋጋ 120

 2

ይህ የሸንቁጥ ልጆች በሚል ርዕስ በአምባሳደር ዓለማየሁ አበበ ሽንቁጥ የተዘጋጀ መጽሐፍ፤ የሸንቁጥ ልጆች የሚላቸው የመሪነት ሚና ኖሮአቸው የተተረከላቸውን ግራዝማች (በኋላም ደጃዝማች) ተሾመ ሽንቁጥን፣ ልጅ ኃይሌ ሸንቁጥ፣ ልጅ አበበ ሸንቁጥ፣ (በኋላም ደጃዝማች)፣ ልጅ ይነሱ ሸንቁጥንና ልጅ ጥላሁን ሸንቁጥ የተባሉትን ወንድማማቾች ነው፡፡

                                                                                                                                 አህመድ ሀሰን (ዶ/ር)

                                                                               በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ዳሬክተር

ከመጽሐፉ ጥንካሬዎች መካከል አንዱ ታሪኩ የቀረበበት ሐቀኝነት ነው፡፡ ለዚህም እንደማሣያ ከሚሆኑት መካከል፤ “አርበኞች ብትንትናቸው ወጣ “ለአርበኞች መሪር ኅዘን ሆነ፡፡” እጅግ የከፋ ዉጊያ ተካሄደ”፣ “የጠላት ጦር በመጨነቁ ከምሽጉ ብቅ ማለት አቅቶት ነበር፡፡”፣ “የጠላት ጦር አሻግሮ ሲመታቸው አርበኞች ብትንትናቸው ወጣ” እና የመሳሰሉት አገላለጾች ናቸው፡፡

ሰልጠነ ስዩም (ዶ/ር)

የአርበኝነት ዘመን ታሪክ ተመራማሪ

ዓለማየሁ አበበ፣ የሸንቁጥ ልጆች አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ ISBN 978994-452705 ገጽ 141 ዋጋ 50

3

The participation of communities in the formulation of strategies for the proper management of local resources under varying conditions, including climate change , this Book clearly addresses this important aspect of local resource management with respect to the choke mountain Range’ which in turn is a major water source of the water flow of the Abay (Blue Nile). In addition to, the book will serve as an important source of information for resource management in general, as well as, serves as teaching material and reference in mountain ecosystem management. It is hence, a recommendable reading by all who endeavor to make a difference in the livelihoods of communities residing in the Abay water shed and in similar ecosystems elsewhere.

 

Shibru Tedla

Professor Emeritus of Bilology

Belay simane Building community Resilience to climate Change AAU Press ISBN 9-78999-4452712 Page 302 Price 90

 4

 ….. አሁን ለአንባቢ በቀረበው መጽሐፍ ውስጥ በዝርዝር የተገለጸው የኢትዮጵያና የእንግሊዝ ሶማሊላንድ የወሰን መደንገግ ታሪክ የተለየ አብነት አለው፡፡ ይህውም ወሰኑ መደንገጉ ብቻ ሳይሆን ሂደቱ በሚያስገርም ምልኣትና ጥንቃቄ መተረኩ ነው፡፡ መተረኩ ብቻ ሳይሆን ትረካው ከኢትዮጵያ ወገን በኢትዮጵያው ቋንቋ መሆኑ ነው… ሌላው በኔ ግምት ለሁኔታው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረገው ደግሞ ብላታ መርስዔ ኀዘንን የመሰለ ጥንቁቅ ምሑር የኮሚሲዮኑ ዋና ጸሐፊ ሆነው መመደባቸው ነው፡፡ እሳቸው በጥንቃቄ ያደራጁትና ይዘው ያቆዩት ዘገባና አባሪ ሰነዶች ናቸው (አዘጋጁ ጥረት ከተሰበሰቡት አባሪዎች ጋር በመሆን) አሁን ለኅትመት የበቁት፡፡

ባሕሩ ዘውዴ

የታሪክ ኤመሪተስ ፕሮፌሰርለ

እኔ ትውልድ ብላታ መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ አዲስ ሰው አይደሉም፡፡ ገና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በነበርንበት ጊዜ የአማርኛ ሰዋሰው የሚለው መጽሐፋቸው መማሪያችን ስለነበረ ከሰማቸው ጋር በደንብ እንተዋወቃለን፤…ገና እኔ በተወለድሁበት ዓመትም በኢትዮጵያና በብሪታንያ ሶማሊላንድ ወሰን መካለሉ ሥራ ተሳትፈዋል…፡፡አንድ የሚያስደንቅና መነገርም ያለበት ነገር አለ፤ በብሪታንያ ሶማሊላንድና ኢትዮጵያ መካከል የተደረገውን ዓይነት መካለል በደቡብ ከኢጣልያ ሶማልያ ጋርና ከኬንያ ጋር፤ በምዕራብ ከሱዳንጋር አልተደረገም፡፡የብላታ መርስዔ ሀዘን ልጅ አምኃ ይህንን ቢያንስ ሃምሳ ዓመት የዘገየ ታሪክ ለሕዝብ እንዲቀርብ በማድረጉ ከፍተኛ ምስጋና ይገባዋል፤ ምናልባትም ለሌሎችም አርአያ ይሆናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም

  የኢትዮጵያ የእንግሊዝ ሱማሌላንድ የወሰን መከለል ታሪክ: አመሀ መርስኤ ሀዘን ወ/ጨርቆስ የገጽ ብዛት 357 ISBN 9-789994-452712
 5

የዶ/ር ደጃዝማች ዘውዴ ጽኑ ተስፋ የኢትዮጵያና የኤርትራ ሕዝቦች አንድነት ነበር፡፡ ገና በመጽሐፉ መግቢያ ላይ፤ የሁለቱን ሕዝቦች ዘመናት- ዘለል ቁርኝት እንዲህ ያሰምሩበታል፡፡ ለኢትዮጵያውም ሆነ ለኤርትራዊ ከጥንት ጀምሮ መሰረታዊ ኃይል ሆኖ ያስተሳሰረውን የጋራ ታሪኩን፤ ዛሬ አዘለውም አቀፈውም፤ ከላዩ የማይወርድ የእኩል ሽክሙ ነው፡፡

 

አሁን በሥልጣን ላይ ያሉት የብዙዎች ኤርትራውያን ወላጆች የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝብን ወድማማችነትና አንድነት በእጅጉ የሚያምኑ ነበሩ፡፡ ስለዚህ እምነታቸውም ታግለውና ተጋድለው ነበር፡፡ ያሁኑ የጎልማሳ ኤርትራውያን ልጆች፣ የወላጆቻቸውን ወይም የአያቶቻቸውን ፈለግ ለመከተላቸው ገና መጪው ታሪክ የሚያሳየው ይሆናል፡፡ ዶ/ር ደጃዝማች ዘውዴ መጽሐፋቸውን በሦስተኛው ክፍል ይዘት ማሳረጋቸው ግን የሳቸውን ጽኑ እምነትና ምኞት የሚያመላክት ነው፡፡

ኃይሉ ሀብቱ ዶ/ር

የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

…..ኤርትራ ነፃነቷን ካወጀች በኋላ ኤርትራን በሚመለከት ከኢትዮጵያ ውጭም፣ በኢትዮጵያ ውስጥም እና ኤርትራ ውስጥም የሚወጡት መጣጥፎች ከሞላ ጎደል በሙሉ ማለት ይቻላል የኢትዮጵያን ዕይታ እንደመዘንጋታቸው፤ ይህ መጽሐፍ ግን የተረሳውን የኢትዮጵያ ዕይታ እንደገና ስለሚያቀርብልን ፋይዳው ላቅ ያለ ነው፡፡

… ኤርትራ (ከጉባት) ጀምሮ እስከ 20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መገባደድ ድረስ የኢትዮጵያ አንድ ክፍል ሆኖ መቆየቱን የሚያሳይ ጽሑፍ በመሆኑ፤ ለኢትዮጵያ አንባብያን ሰፊ ትምህርት ይሰጣል፡፡

… መጽሐፉ በዘመናዊ ኤርትራና ኢትዮጵያ ከፍ ያለ ሚና የተጫወቱ ሰዎችን አጫጭር የሕይወት ታሪክ መያዙም ለመላው አንባቢ እና በተለይም ለመምህራን ለጋዜጠኞች በምንጭነት ያገለግላል፡፡

ሺፈራው በቀለ (ፕሮፌሰር)

የታሪክ ትምህርት ክፍል

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

 

  የኢትዮጵያና የኤርትራ ግጭት በዶ/ር ዘውዴ ገ/ስላሴ 2007ዓ.ም ISBN 9-789994-452651 አ.አ.ዩ.ፕሬስ ዋጋ 100 ብር የገጽ ብዛት 330

6

ስደት የሰው ልጅ በማኅበር መኖር ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ያልተለየው ዕጣ ፈንታ ነው፡፡ ምክንያቶች ተፈጥሯዊ ወይም ማኅበረሰባዊ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ መጠኑ ሊበዛም ሊያንስም ይችላል፡፡ የኢትዮጵያ ታሪክም ኢትዮጵያውያን በተለያየ ምክንያት ካገራቸው ለመሰደድ የተገደዱበት ዘመን ነበር፡፡

አሁን ለሕትመት የበቃው የተስፋዬ መጽሐፍ የዚህ ታሪክ አንድ ምዕራፍ ስዕላዊ በሆነና ቀልብን በእጅጉ በሚስብ መንገድ ይተርካል፡፡ ወቅቱ የ1960ዎቹ ዓመታት የኢትዮጵያ ተማሪዎች የትግል ታሪክ ከፍተኛ ደረጃ የደረሰበትና ከመንግስት ጋር ያደርጉት የነበረው ፍልሚያ ጣራ የነካበት፣ በለተይ በታህሳስ 1962 የተማሪዎች መሪ ጥላሁን ግዛው ከተገደለበት በኋላ በተማሪዎች ንቅናቄ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ የነበራቸው ተማሪዎች ከጸጥታ ኃይሎች ወከባ ለማምለጥ የነበራቸው ምርጫ ስደት ነበር፡፡

ባሕሩ ዘውዴ የታሪክ ኤሜሪተስ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

  የስደታችን ትውስታ በተስፋየ ዘርፉ 2007 ዓ.ም ISBN 9-789994-452590 አ.አ.ዩ.ፕሬስ ዋጋ 50 ብር የገጽ ብዛት 184
 7

The book is designed for those taking Biophysics course for the first time. It has basic concepts on thermodynamics, chemistry and a little bit of biochemistry to show how biophysics is linked to the there areas.Key features̏It illustrates concepts of energy and how different types of weak bonds play vital roles in biological systems.̏It touches upon the physical laws that are applicable to living systems̏Some insets (ideas linked to the text but are slightly requiring additional knowledge of physics of chemistry) are also given for motivated readers.

  Text Book Of Biophysics በ ገላና አመንቴ 2015 GC ISBN 9-789994-452606 አ.አ.ዩ.ፕሬስ ዋጋ 127 ብር የገጽ ብዛት 434
 8

Ethiopia has rich tradition in educating its youth, asserts the conventional wisdom yet there is also a strong complaint that those roots are ignored. This publication does not follow up this debate but presents studies on the traditional Ethiopian education with the hope that students in education studies would appreciate what our tradition can offer or does not offer in the way of socializing and integrating the youth into the society. These studies are: ባህልና ዕድገት discussing the influence of tradition; “The Education of Adwa Fighters” reflecting incidental military education; studies on formal religious education of Orthodox Church and Muslim communities namely የቤተ ክህነት የቀለም ትምህርት and የቤተመስጊድ ትምህርትና ሥርዓቱ with the case studies ጥንታዊ ትምህርት ዘአዲስ ዓለም በደብረጽዮን and the Traditional Language Teaching: the Case of Quran Schools, Education magic in traditional Ethiopia, “the reflections on ተግባረ ጥበብና ቀለም ትምህርት፤ የቀለም ትምህርት መሪ ሀሳቦች and ባህላዊ የቤተክህነት ትምህርት ከየት ወዴት? Social Studies in Ethiopia are presented as a contrast to socialization based on religious and patriarchal profession association and its role in changing the traditional polity.

Most of the studies are conducted while this writer was teaching the course social foundation of Ethiopian education at the faculty of education Addis Ababa University.

  ባህልና ትምህርት በኢትዮጵያ በ ኃይለ ገብርኤል ዳኜ 2007 ዓ.ም ISBN 9-789994-4526፪ አ.አ.ዩ.ፕሬስ ዋጋ 100 ብር የገጽ ብዛት 359
 9

Textbook of Economic Geology is a book written in a very concise and clear manner where the different groups of ore deposits are clearly put in terms of their geologic and tectonic setting. Such approach and apply the same knowledge to mineral exploration success. The book is timely and the only book available in local market for the mineral industry in Ethiopian.

 

Zerihun Desta, PhD Economic geologist

General Manager. Ethiopian Mineral Resource Development S.C.

Text Book Of Geology በ ወራሽ ጌታነህ እና ሠለሞን ታደሰ 2015 GC ISBN 9-789994-452583
አ.አ.ዩ.ፕሬስ ዋጋ 70 ብር የገጽ ብዛት 306
 10

የዚህ መጽሐፍ መታተም የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋን ለመማርና ማስተማር ፍላጎት ያላቸው ሁሉ ሥልጠናው ምን ዓይነት መልክ ሊኖረው እንደሚገባ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ስለሚረዳቸው፤ ብቃት እና የማሠልጠን ምስክር ወረቀት ባላቸው አሠልጣኞች የመማር መብታቸውን እንዲያስከብሩ እንደሚረዳቸው ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

ስለ ኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ማኅበረሰብ ታሪክ፤ ቋንቋ ማስተማሪያ መንገዶች ግንዛቤ ለመጨበጥ የሚፈልጉ ሁሉ ይህን መጽሐፍ እንዲያነቡ አበረታታለሁ፡፡   ውጤታማ   ለመሆን   የሚያስፈልጉ   የሚሰሙም ሆነ መስማት የተሳናቸው የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ መምህራንም ይህን መጽሐፍ እንደ ዋነኛ መመሪያ እንዲጠቀሙበት አጥብቄ እመክራለሁ፡፡

 

ተክለሃይማኖት ደርሶ

የመጀመሪያው የመስማት የተሳናቸው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ፤ የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ማኅበር መሥራች አባላት እና የመጀመሪያው የምልክት ቋንቋ መዝገበ ምልክት አዘጋጅ ኮሚቴ አባል

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ በ ጳውሎስ ካሡ 2007 ISBN 9-789994-452620 አ.አ.ዩ.ፕሬስ ዋጋ 50 ብር የገጽ ብዛት 221
11

Interviewing the last witnesses of the blood both of Debre Lebanon’s deserves the utmost gratitude of all Ethiopians.

H.H Lid Alfa worsen asserted, Dr. Phil Honorary sensor of the University of Tubingen Lisboans deserves the utmost gratitude of university of Tubingen Charming of the Board of patrons of orbits aethiopicus the society for the preservation and promotion of Ethiopian Culture. Having dedicated many years of his life to the reconstruction of this tragic event, Ian Campbell has been able to detail the various stages of the massacres, minute by minute with extraordinary precision the story is almost unbelievable full of masquerade deceit, false promises, and careful preparations for choosing the site for conducting the massive exactions tremendous

 

violence, robberies of the churches and exchanges of telegrams between grazing and mallets to closely coordinate the schedule of the slaughter. The organization of the crime is so prefect that the religious are not able to escape unable to even consider rebelling they passively awaits their death. And their cadavers fall in hundreds in to the saga weed gorge, thrown to hyenas and vultures.

Professor Angelo Del Boca

Torino

Italy

The Massacre of Debre Libanos Ethiopia 1934 By Ian Campbell 2014 GC ISBN 9-789994-452514
አ.አ.ዩ.ፕሬስ ዋጋ 100 ብር የገጽ ብዛት 307 

For more Books Briefing details please see the attachment below :