AAU Housing Competition
![](https://www.aau.edu.et/wp-content/uploads/2023/12/logo.png)
ለአዲስ አባበ ዩኒቨርስቲ ለአካዳሚክ ሰራተኞች በሙሉ
ቤት ለመከራየት በቅያሬም ሆነ አዲስ አመልካቾች የሚከተሉትን ማስረጃዎች በማሟላት ከሚያዚያ 11 እስከ ሚያዚያ 18/2016 ዓ.ም ድረስ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ብቻ በአካል በመገኘት በማንዴላ ህንጻ 3ኛ ፎቅ በሚገኘው በቤቶች አስተዳደር ቢሮ 310 መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ለምዝገባ በምትመጡበት ወቅት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡
- አሁን በሥራ ላይ ለመሆንዎ ከሰው ሀብት ዳሬክተር የተጻፈ ደብዳቤ
- የኃላፊነት ደረጃ የተሾሙበት ደብዳቤ
- የአገልግሎት ዘመን
- የጋብቻ ሁኔታ
- የቤተሰብ መጠን
ማሳሳቢያ
- በተራ ቁጥር 1፣ 2፣3፣4 እና 5 ላይ ለተገለጸው ማስረጃ ማያያዝ ያስፈልጋል፣ማስረጃ ያላያያዘ መመዝገብም ሆነ መወዳደር አይችልም፡፡
- ማናኛውም ተወዳዳሪ መምረጥ ያለበት አንድ ሳይት ብቻ መሆኑን እየገለጽን ከተጠቀሰው ቀን ውጪ ምዝገባ የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን ፡፡
ቤቶቹ የሚገኙበት ሳይት
ተ.ቁ | ቤቱ የሚገኝበት ሳይት | የመኝታ ቤት ብዛት | የቤት ብዛት |
1 | ሰፈረ ሳላም እንግዳ ማረፊያ | ባለ 3 መኝታ | 19 |
2 | ›› | ባለ 2 መኝታ | 1 |
3 | ሳር ቤት አሮጌው | ባለ 2 መኝታ | 1 |
4 | ጣና | ባለ 2 መኝታ | 1 |
5 | ፒኮክ | ባለ 2 መኝታ | 1 |
6 | ካሳንችስ | ባለ 2 መኝታ | 1 |
7 | ቶታል 3ቁጥር ማዞሪያ | ስትዲዮ | 1 |
ቤቶች አስተዳደር