Menu

Announcement for 2017 EC Freshman Students

 

 

 

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2017 የትምህርት ዓመት በመደበኛው የቅድመ-ምረቃ ትምህርት መርሃ-ግብር በትምህርት ሚኒስቴርና በዩኒቨርሲቲው የቅድመ-ምረቃ ትምህርት መግቢያ መስፈርት መሠረት ቅበላ ላገኛችሁ ተማሪዎች በሙሉ፡- ጥቅምት 5 እና 6 2017 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ውጪ የምትመጡ ተማሪዎችን ብቻ በየተመደባችሁበት የዩኒቨርስቲው ካምፓሶች የምናስተናግድ መሆኑን እናሳስባለን::

ለሁሉም ተማሪዎች የአዲስ አበባ ነዋሪ የሆናችሁትን ጨምሮ አጠቃላይ ስለ ዩኒቨርስቲዉ ገለፃ (Orientation) ቅዳሜ ጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን ገለጻ የሚደረግባቸውን ቦታዎች ወደፊት እናሳውቃለን፡፡