Menu

Announcement for Freshman Students

 

 

 

ለ2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በመንግስት ስኮላርሺፕ እንዲሁም በግል ከፍላችሁ ለመማር ቅበላ ላገኛችሁ የአንደኛ ዓመት ቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች የወጣ የቅበላ እና ምዝገባ ማስታወቂያ
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2017 የትምህርት ዓመት በመደበኛው የቅድመ-ምረቃ ትምህርት መርሃ-ግብር በትምህርት ሚኒስቴርና በዩኒቨርሲቲው የቅድመ-ምረቃ ትምህርት መግቢያ መስፈርት መሠረት ቅበላ ላገኛችሁ ተማሪዎች በሙሉ፡-
ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትመጡ ተማሪዎች ጥቅምት 5 እና 6 2017 ዓ.ም በየተመደባችሁበት የዩኒቨርስቲው ካምፓሶች በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ
ያሳውቃል፡፡ ተማሪዎች ለምዝገባ ስትመጡ:

  1. 1. የአስራ ሁለተኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ውጤት ዋናውንና ኮፒ፣
    2. አራት ጉርድ ፎቶግራፎች፣
    3. የማደሪያ ምድብ (Dormitory) ለተሰጣችሁ ብርድልብስና አንሶላ እንዲሁም የስፖርት ትጥቅ ይዛችሁ እንድትመጡ ያስታውቃል፡፡

ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትኖሩ ተማሪዎች

  • በዩኒቨርስቲው የተመደበላችሁን የመኝታ ክፍል UAT በተፈተናችሁበት UG ቁጥር በመጠቀም ከታች ባለው ሊንክ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ያሳውቃል፡፡

https://portal.aau.edu.et/NewStudents/DormitoryPlacement

  • በተጠቀሱት ቀናት (ጥቅምት 5 እና 6) ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትመጡ ተማሪዎች በመርካቶ አውቶብስ ተራ፣ በላም በረት፣ በአቃቂ እና በአስኮ የመኪና መናኸሪያዎች ዩኒቨርስቲው የትራንስፖርት አገልግሎት የሚያቀርብ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  • ነዋሪነታችሁ አዲስ አበባ ከተማ ሆኖ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቅበላ ያገኛችሁ ተማሪዎች ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎችና ዶክመንቶች ይዛችሁ ሪፖርት የምታደርጉት ሰኞ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም መሆኑን ያሳውቃል፡፡

https://portal.aau.edu.et/NewStudents/Welcome,   www.aau.edu.et

  • ለሁሉም ተማሪዎች አጠቃላይ ስለ ዩኒቨርስቲዉ ገለፃ (Orientation) ቅዳሜ ጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ.ም ይሆናል፡፡
  • የትምህርት ኮርሶች ምዝገባ ሰኞ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ሲሆን
  • የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያዉ ሰሚስተር ትምህርት የሚጀመረዉ ማክሰኞ ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም ይሆናል፡፡
  • ስለምዝገባ ሂደቶች በተመለከተ እና ተጨማሪ መረጃ ከታች ካሉት ሊንኮች ማግኘት የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን::
    https://portal.aau.edu.et/NewStudents/Welcome
    www.aau.edu.et

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር