Menu

Announcement for Undergraduate Program Applicants who have score 500 and Above

2016 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ብሔራዊ ፈተና ከፍተኛ ዉጤት ላስመዘገባችሁ የተፈጥሮ ሳይንስና በማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ አመልካቾች በመንግስት ስፖንሰርሺፕ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ዕድል ዉድድርን ይመለከታል

በአገር አቀፍ ፈተና ዉጤታችሁ በተፈጥሮ ሳይንስና በማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ 500 እና ከዚያ በላይ የሆነ ዉጤት ያስመዘገባችሁ አመልካቾች አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለመደበኛው ፕሮግራም የዲግሪ መርሐ-ግብር እንድታመለክቱ ይጋብዛል፡፡

ይህንን መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች በ https://portal.aau.edu.et በመግባት Apply for Admission ሊንክ በመጫን መሰረታዊ መረጃዎች ከሞሉ በኋላ sponsorship ለሚለው Government Scholarship የሚለዉን በመምረጥ Other reason የሚለዉ “more than 500 and above” በክፍት ቦታዉ ላይ በመፃፍ የ12ኛ ዉጤት ያስመዘገባችሁበትን የሚያሳይ ማስረጃ ማያያዝ ያስፈልጋል፡፡

  1. የማመልከቻ ጊዜ ሐሙስ መስከረም 9 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 1፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12፡00 ሰዓት ድረስ ይሆናል
  2. ይህ ጥሪ ከዚህ ቀደም ያመለከቱት አመልካቾች አያካትትም

አ.አ.ዩ ሬጅስትራር