Menu

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2017 ዓ.ም. በቀን በመደበኛ መርሃ ግብር በመንግስት ስኮላርሽፕ እና በግል ከፍለዉ ለመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት አመልካቾች

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2017 ዓ.ም. በቀን በመደበኛ መርሃ ግብር በመንግስት ስኮላርሽፕ እና በግል ከፍለዉ ለመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት አመልካቾች

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ2017 ዓ.ም ቅድመ ምረቃ በመደበኛ መርሃ ግብር ትምህርት ሚኒስቴር ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምደባ ስለማያካሂድ በመንግስት ስኮላርሺፕ እንዲሁም በግል ከፍላችሁ በዩኒቨርሲቲያችን መማር ለምትፈልጉ የዩኒቨርሲቲዉን የመግቢያ ፈተና (UAT) እና ዩኒቨርሲቲዉ ያወጣዉን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኋል፡፡
በዚህም መሠረት በዩኒቨርሲቲዉ ድረ ገጾች (www.aau.edu.et ወይም https://portal.aau.edu.et) ላይ የተመለከቱትን ዝርዝር የማመልከቻ መስፈርቶች
በማሟላት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡
 የመመዝገቢያ ቀናት እስከ መስከረም 08/ 2017 ዓ.ም ድረስ ይሆናል
 የዩኒቨርሲቲዉ የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀናት ወደፊት በዩኒቨርሲቲዉ ድረገጾች ላይ ይገለጻል::

አ.አ.ዩ ሬጅስትራር