አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2017 ዓ.ም. በማታ መርሃግብር ለመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት አመልካቾች
የሚከተሉትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል
1. ከ2012 እስከ 2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈትነዉ ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መስፈርት መሰረት ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያ የመቁረጫ ነጥብ የሚያሟላ/የምታሟላ፤
2. በዲግሪያችሁ ለምታመለክቱ የወጪ መጋራት ያጠናቀቃችሁበትን የሚገልፅ ደብዳቤ ከትምህርት ማስረጃ ጋር ማቅረብ
3. ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ከ2014-2016 ዓ.ም በተለያየ ምክንያት አቋርጣችሁ ለምታመለክቱ የወጪ መጋራት ያጠናቀቃችሁበትን የሚገልፅ ደብዳቤ ከትምህርት ማስረጃ ጋር በማያያዝ ማቅረብ
4. የዲፕሎማችሁን ወይም ደረጃ 4 ትምህርት ማስረጃ ከCOC ደረጃ 4 ጋር ማቅረብ
5. በ2016 ዓ.ም በተለያዩ የትምህርት ተቋማት የሪሚዲያል ትምህርት ተከታትሎ/ተከታትላ ፈተና ያለፈ/ያለፈች
በዚህም መሠረት በዩኒቨርሲቲዉ ድረ ገጾች (www.aau.edu.et ወይም https://portal.aau.edu.et) ላይ የተመለከቱትን ዝርዝር የማመልከቻ መስፈርቶች
በማሟላት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡
የመመዝገቢያ ቀናት እስከ መስከረም 08/ 2017 ዓ.ም ድረስ ይሆናል
የዩኒቨርሲቲዉ የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀናት ወደፊት በዩኒቨርሲቲዉ ድረ
ገጾች ላይ ይገለጻል::
አ.አ.ዩ ሬጅስትራር