በመንግስት ስኮላርሽፕ ለመጀመሪያ ዲግሪ ማስረጃ ማያያዝን ይመለከታል
በቀን መደበኛ መርሃ ግብር በመንግስት ስኮላርሽፕ ለመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት ለማመልከት ከተጠየቁት መስፈርቶች አንዱ የቤተሰብ የገቢ መጠንን የሚገልፅ ማስረጃ ማያያዝ መጠየቃችን ይታወሳል፡፡
በዚህ መሰረት
1. ከወረዳ ወይም ከቀበሌ ወይም መስሪያ ቤት ስለገቢያቸዉ ዝቅተኛነት የሚገልፅ ማስረጃ ከሚመለከተዉ ከወረዳ ወይም ቀበሌ ወይም መስሪያ ቤት ዘርፍ ኃላፊ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
2. የቤተሰቡ ኃላፊ በጡረታ ላይ የሚገኙ መሆናቸዉን የሚገልፅ ደብዳቤ ወይም የታደሰ የጡረተኝነት መታወቂያ ወይም የባንክ ደብተር ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
አ.አ.ዩ ሬጅስትራር