Menu

Admission of Self-sponsored Students in the Regular Undergraduate Program for the 2023_24 Academic Year

 

 

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

ለ2016 ዓ.ም. ለመጀመሪያ ዲግሪ በመደበኛ መርሃ-ግብር የትምህርት ክፍያ በመክፈል መማር ለሚፈልጉ አመልካቾች በሙሉ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2016 የትምህርት ዓመት በመንግሥት የተመደቡ ተማሪዎች ተቀብሏል:: ይሁንና በጣም በተወሰኑ የትምህርት መስኮች በተመጠነ መልኩ የግል አመልካቾችን ለመቀበል ዝግጅት አድርጓል፡፡ አመልካቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት ማመልከት እንደሚችሉ በደስታ ይገልፃል፡፡

  1. በ2015 አና 2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈትነዉ ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መስፈርት መሰረት ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያ የመቁረጫ ነጥብ የሚያሟላ/የምታሟላ፤
  2. አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለቅድመ ምረቃ ተማሪዎች መግቢያ የሚያወጣዉን የመግቢያ ፈተና (UAT) ተፈትኖ/ና መቁረጫ ነጥቡን የሚያሟላ/የምታሟላ፤
  3. በ2015 ዓ.ም. በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ተምራችሁ ለምታመለክቱ የወጪ መጋራት ያጠናቀቃችሁበትን የሚገልፅ ደብዳቤ ከትምህርት ማስረጃ ጋር በማያያዝ ማቅረብ
  4. ዩኒቨርሲቲዉ በ12ኛ ብሔራዊ ፈተና ዉጤት መሠረት ድልደላ ሲያካሒድ  በመረጠው/የመረጠችው የትምህርት ፕሮግራም አማራጮች ውስጥ ለመደልደል ወጤቱ ካላበቃው/ካላበቃት ዩኒቨርሲቲዉ ወደፊት በሚያደርገው ድልደላ ከሌሎች ተማሪዎች ጋር ተወዳድሮ/ተወዳድራ ለመደልደል ፈቃደኛ የሆነ/ች፤
  5. ለጤና የትምህርት ዘርፎች ዩኒቨርሲቲዉ የሚጠይቀዉን ተጨማሪ ምዘና ማለፍ የሚችል/የምትችል፤

የማመልከቻ ቀናት ከህዳር 20 እስከ ህዳር 25 ቀን 2016 ዓ.ም ሲሆን የማመልከቻ ሒደቱን እንደሚከተለው ማካሔድ ይጠበቅባቸዋል፤

  1. ለመግቢያ ፈተና (UAT) ለመመዝገብ እና የትምህርት ፕሮግራሞችን ለመምረጥ የዩኒቨርሲቲዉን ድረ-ገጽ ላይ (https://portal.aau.edu.et/ >>>Apply for Admission) በመጎብኘት ምዝገባውን ማካሔድ የምትችሉ ሲሆን ፖርታሉ የሚያወጣውን ጉርድ ፎቶግራፋችሁ ያለበትን የመፈተኛ መግቢያ ትኬት በማተም መያዝ ይጠበቅባችኋል፤
  2. ለመግቢያ ፈተና ለመመዝገብ ዩኒቨርሲቲው ከሚሰጣቸው የተለያዩ የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራሞች አምስቱን የትምህርት ፕሮግራሞችን በፍላጎት ቅደም ተከተል በጥንቃቄ መምረጥ ይገባችኋል፤
  3. ዩኒቨርሲቲዉ የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ጊዜ ከህዳር 27 እስከ ህዳር 28 2016 ዓ.ም ሲሆን ወደፊት በዩኒቨርሲቲዉ ድረ-ገፅ በሚወጣው ዝርዝር መርሐ-ግብር መሰረት እንዲሁም የዩኒቨርሲቲዉን የፈተና ማዕከል (Testing Center) የቴሌግራም ቻናል https://t.me/aauGAT በመከታተል በፈተናው ቀንና ሰዓት በመፈተኛ ቦታው በመገኘት ፈተናዉን መዉሰድ ይኖርባችኋል፤
  4. በመደበኛ መርሃ-ግብር ለመግቢያ ፈተና እና ለምዝገባ 750 (ሰባት መቶ ሃምሳ ብር) በቴሌ ብር መክፈልና ፖርታሉ ላይ በተሰጠው መመሪያ መሠረት የክፍያ ማረጋገጫ ቁጥሩን ማስገባት ይኖርባችኋል፤
  5. የመግቢያ ፈተና ዉጤት በዩኒቨርሲቲዉ ፖርታል (https://portal.aau.edu.et) የማመልከቻ ቁጥራችሁን በማስገባት ማየት የሚቻል ሲሆን የፈተናዉን የመቁረጫ ነጥብ ያሟላችሁ የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን በአካል ይዞ ስድስት ኪሎ በሚገኘዉ የሬጅስትራር ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 በመቅረብ ማስገባት ይጠበቅባችኋል፤
  6. ሌሎች ዝርዝር መረጃዎችን በዩኒቨርሲቲዉ ድረ-ገጾች (http://aau.edu.et እና https://portal.aau.edu.et) ወደፊት የሚለቀቁ መሆናቸዉን እናሳዉቃለን::

ማሳሰቢያ

  • የተማሪዎች ቁጥር ከመቀበል አቅም በታች (ዝቅተኛ) የሆነበት የትምህርት ፕሮግራም የማይከፈት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር

See List of Undergraduate Programs Below:

Download (PDF, 116KB)