Menu

New Anti-Plagiarism software

 

 

የአድስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአለም ቀዳሚ የሆነ የፕላጃሪዝም ሶፍትዎር ለራሱና ለሌሎች 13 ተቋማት ጥቅም እንድዉል አስተዋወቀ

የአድስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ላለፉት ሶስት አመታት የፕላጃሪዝም ሶፍትዌር ተግባራዊ ማድረጉ ይታወቃል፡፡ በአሁኑ ወቅት ከኦቶኖሚ ዝግጅት ጋር ተያይዞ ብዙ ማሻሻያዎችን በማድረግ ላይ ያለ ሲሆን ከነዚህም አንዱ የሆነው ከዚህ በፊት የምንጠቀምበትን የፕላጃሪዝም ሶፍትዌር በማሻሻል በአለም አቀፍ ደረጃ ቀዳሚ የሆነውን Turntin ሶፍትዌር ከሌሎች 13 ዩኒቭርሲቲዎች ጋር ገዝቶ ለአገልግሎት ዝግጁ አድርጓል። የአሰልጣኞች ስልጠናም ለሁለት ተከታታይ ቀናት በኦንላይን ተከናውኗል፡፡

በአሁኑ ሰኣትም ለስራተኞች ስልጠና ለመስጠት የዩኒቭርሲቲው አብያተ መጽሀፍት ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ በዚህ ወቅት ተግባራዊ የተደረገዉ ሶፍትዌር ከ 99.3 ቢሊዮን በላይ ዳታቤዝ፤1.6 ቢሊዮን ከዚህ በፊት የተሰሩ ስራዎችና ከሁሉም ኦንላይን ላይ ካሉ ሶርሶች ጋር በማወዳደር የሚሰራ ሲሆን ከዚህ በፊት ከነበረው ከፍተኛ መሻሻል የሚያመጣ ነው፡፡ በተጨማሪም ሲስተሙ በ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የተሰሩ ስራዎችን መለየት የሚችል ሲሆን በከፍተኛ ትምህርት ውስጥ የሚሰሩ ምርምሮችን ጥራት በመጨመር ረገድ ከፍተኛ አስተዋኦ ያደርጋል ተብሎ ይገመታል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ሌሎችም ተቋማት ተመሳሳይ አሰራር እንድከተሉ የሚያግዝ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ማሳወቅ ይፈልጋል፡፡