Menu

condolences

ዜና እረፍት

1920-2013

የኢትዮጵያ የሽግግር መንግስት ም/ፕሬዘዳንት የነበሩት አምባሳደር ዶክተር ፈቃዱ ገዳሙ ታመው በህክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ93 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ አምባሳደር ዶ/ር ፈቃዱ ገዳሙ ረጅሙን አገልግሎት የሰጡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሲሆን፤ በ1983 ዓ.ም በሽግግር መንግስት በም/ፕሬዘዳንትነት ከማገልገላቸውም በላይ፤ በካናዳ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግስት ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር በመሆን አገለግለዋል፡፡ አምባሳደር ዶ/ር ፈቃዱ ገዳሙ በትዳር ዓለም በቆዩበት ወቅት 3 ወንዶችን 2 ሴቶችን አፍርተዋል፡፡ የአምባሳደር ዶ/ር ፈቃዱ ገዳሙ የሽኝት መርሀ-ግብር አርብ ነሀሴ 7 ቀን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከተካሄደ በኋላ፤ የቀብራቸው ስነ-ስርዓት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፤ ቤተሰቦቻቸው፤ወዳጅ ዘመዶቻቸውና የቀድሞ የስራ ባልደረቦቻቸው በሚገኙበት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ከቀኑ በ6 ሰዓት የሚፈፀም መሆኑን እናስታውቃለን፡፡